የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገለግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የሚደረግ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገለግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የሚደረግ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጧል።
በክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ በአቶ ኢብራሂም ተማም የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የወልዴሃኔ ጤና ጣቢያ ጉብኝተዋል።
ጉብኝቱ የጤና ተቋማትን በቅርበት በመደገፍና በመከታተል ተቋማቱ ለማህበረሰቡ ተገቢውን የጤና አገለግሎት እንዲሰጡ ማስቻል እንደሆነ የቢሮው ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም አስረድተዋል።
አቶ ኢብራሂም አክለውም ጤና ጣቢያዎች በተለይ ከጤና መረጃ አያያዝና አላላክ፣ ከመድሀኒት ቁጥጥርና አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ጤና ጣቢያዎች የማህበረሰቡን ጤና ከመጠበቅ አንፃር ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁ ሀላፊው በተቋሙ የሚገኙ ባለሙያዎችና ሀላፊዎች ማህበረሰቡን በታማኝነትና በቁርጠኛነት ማገልገል ይገባቸዋልም ብለዋል።
ከወልደሃኔ ጤና ጣቢዬ እንደ ማነቆ የተነሱ ጉዳዮችን ለመፍታት ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጧል።
ቢሮው በሁሉም አከባቢዎች ለሚገኙ ጤና ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፋዊ ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተብራርቷል።
በጉብኝቱ የክልሉ ጤና ቢሮ አቶ ኢብራሂም ተማምን ጨምሮ በቢሮው የጤናና ጤና ነክ ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክቴር አቶ ሙሉቀን አሰፋ እንዲሁም ሌሎች የዞንና የወረዳ የባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።