የጤና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስራዎች ላይ አተገባበር ላይ ለዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናው በተዋረድ እስከ ታችኛው ጤና ተቋማት ድረስ ለባለሙያዎች አስፈላጊነቱ መሠረታዊ የህ/ሰብ ጤና አደጋዎች የመለየት ምላሽ ላይ ህ/ሰቡን የማስተባበር አቅም እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
የጤ ቢሮ ጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያ የሆኑት አቶ እንየው ከበደ እንደገለጹት ስልጠናው ከዚህ በፊት ስልጠናውን ላላገኙ የዞን የወረዳ እና የጤና ተቋማት ባለሙያዎች እየተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የዘርፉ ባለሙያዎች የጤና አደጋዎችን ቀድመው በመለየት፣ የመዘጋጀት እንዲሁም አደጋዎች ሲከሰቱ ደግሞ ፈጥኖ ምላሽ የመስጠት አቅም በየደረጃው እንዲኖራ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል አቶ እንየው።
እንደ ክልል እየተከሰቱ እና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችና አደጋዎች ላይ ባለሙያዎቹ በቂ ትኩረት በማድረግ መስራት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የእነዚህ መረጃዎች አያያዝ፣ ጥራት እና ወቅታዊነት የዘርፉ ቁልፍ ተግባር እንደሆነም ጠቅሰዋል።
የጤ ቢሮ ጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች በተወከሉበት ተግባራቸውን አከናውነው ምላሽ ለመስጠት እና ዘርፉን ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጂት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል አቶ እንየው።