የጨና ወረዳን በጤና ተግባራት ሞዴል ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የጨና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አስተወቀ

በጤና ተግባራቸው ሞዴል የሆኑ ሁለት የሴቶች የልማት ህብሬቶች በቦባ ቆጫ ቀበሌ መመረቃቸውም ታውቋል።
በምረቃ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የጨና ወረዳ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አብነት ሲዓ እንደተናገሩት የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ የማህብረሰቡን ጤና ማስጠበቅና ከቆሻሻ የፀዳ አካባቢ ለመፍጠር መሆኑን ገልጿል።
ይህንን መነሻ በማድረግ በወረዳው ሁሉንም ቀበሌዎች በ2016ዓ/ም ሞዴል ቀበሌዎችን ለመፍጠር ታቅዶ የተሰራ ቢሆንም በወባ ወረርሽኝ ምክንያት ስራው መጓተቱን ያስታወቁት ወ/ሮ አብነት በ2017ዓ/ም እስከ መስከረም 30 ድረስ 5 ቀበሌዎችን እንዲሁም እስከ ታህሳስ 30/2017ዓ/ም ድረስ ሁሉንም ቀበሌዎች ሞዴል ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የሴቶች ልማት ቡድን መሰረት በማድረግ የተጀመረ ሞዴል የማድረግ በቦባ ቆጫ ቀበሌ ጭታ-2 እና 3ት ሴቶች ልማት ቡድኖች ተመርቀው ለሌሎች ሞዴል መሆናቸውን ገልጸዋል።
18ቱን የጤና ፓኬጆችን በመፈጸም ሞዴል ለሆኑት በኦርቢስ ኢንተርናሽናል ፕሮጀክት ድጋፍ ዘመናዊ የሽንት ቤት መክደኛ መበርከቱንም አስታውቀዋል።
ለዚህ ተግባር ውጤታማነት የድርሻቸውን የተወጡ አካላት ያመሰገኑት ኃላፊዋ አሁንም ጤንነቱ የተጠበቀ ማህብረሰብ ለመንገባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሁሉንም የጤና ተግባራትን በውጤታማነት በመምራትና በመፈፀም የህ/ሰቡን ጤና ማስጠበቅ የቅድሚያ ተግባር ነው ያሉት ሀላፊው በሁለቱ ልማት ህብረቶች የታዩ ጠንካራ ሥራዎች ወደ ሌሎች መስፋት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የቀበሌው ሁሉ አቀፍ ስራዎች ደጋፊ አመራር አቶ ክፍሌ ገ/ስላሴ በበኩላቸው በቀበሌው ሁሉን ተግባራት ውጤታማት ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የጤና ተግባር ቀዳሚ መሆኑን ገልጿል።
ዛሬ በቀበሌዎች በሁለት ልማት ህብሬቶች ላይ የታዩውን ምርጥ ተሞክሮ ወደ ቀሪ ልማት ህብረቶች በማዳረስ በተያዘው ቀን ቀበሌውን በጤና ሞዴሎ አድርጎ ለማስመረቅ እየተሠራ መሆኑን ገልጿል።
የግል እና የመንገድ ዳር ሽንት ቤቶች፣የአጎበር አጠቃቀም፣ የፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶች፣የእቃ መደርደሪያዎችና ሌሎች ሞዴል ሥራዎች በምረቃ ተሳታፊዎች ተጎብኝቷል።
በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አብነት ሲዓ፣የዋቻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተረፈ አዴሎ፣የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች፣የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የልማት ህብሬቱ መሪዎችና ነዋሪዎች ተሳትፏል።
ዘገባው ጨና ወረዳ የመ/ኮሙኒኬሽን ነው።