የጪዳ ጤና ጣቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አሰጣጡ እየተሻሻለ እንደሆነ ተገለፀ ::
በጪዳ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጪዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገለግሎት አሰጣጡን አያሻሻለ እንደሆነ በጤና ጣቢያው ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች ገልፀዋሉ።
ጤና ጣቢያው በፊት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታይባቸው የነበረው ችግሮች መቀረፍ መቻሉን ነው ተጠቃሚዎች የገለፁት።
በተለይ ከጤና መድህን አጠቃቀም ላይ ከዚህ በፊት ክፍተቶች እንደነበሩና ባለሙያዎች ጤና መድህን ለያዙት ግለሰቦች አስፈላጊውን መድኃኒት እንደማይሰጡና አሁን ግን ሁሉንም መድኃኒት በጤና ጣቢያው እያገኙ እንዳሉ ነው የጠቆሙት።
የወባ በሽታ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በከፍል የመቀነስ አዝማምያ መታየቱን የገለፁት የጪዳ ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ከበደ ብርሃኑ ማህበረሰቡ ስለ ወባ በሽታ ግንዛቤ በተሰጠው ልክ እየተከላከሉ እንዳሉ ገልፀው የመከላከል ስራው ተጠናክረው ይቀጥላል ብለዋል።
የወረርሽኙ መቀነስ ከክልል ጀምሮ ስለተደረገው የመድኃኒት ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተለይ በቅርቡ የቦርድ ግምገማ ከተደረገ ወዲህ ጥሩ መሻሻሎች እንዳሉ የገለፀው ሀላፊው በግምገማ ወቅት ቃል የተገቡ ነገሮች ለጤና ጣቢያው ወሳኝ ነገሮች በመሆኑ ተፈፃሚ ቢሆኑ የሚል ጥያቄም አቀርበዋለሁ።
የወባ ወረርሽኝ ለመቀነስ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ወዳሉባቸው ቀበሌዎች ባለሙያዎችን በመመደብ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ያሉት ዶ/ር ፋይሰል ይማም በሽታው ሙሉበሙሉ እስከምጠፋ የባለሙያዎች ድጋፍ ይቀጥላልም ብለዋል።
አንዳንድ በላብራቶሪ ክፍል ካርዶችን የማቆየት ሁኔታ እንደ ክፍተት ይነሳል ያሉት ተጠቃሚዎቹ በጤና መድን እያገኘን ያለው አገለግሎት ከከፍተኛ ሀብት ብክነት የታደገ ስለመሆኑ መንግስትን አመስግነዋሉ።
ዘገባው የጪዳ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው።