የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛ።

ከየካቲት አጋማሽ 2017 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት በሁሉም ዞንና ወረዳዎች ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት በዘመቻ መልክ የሚሰጥ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልሰኩ እንደሚሰራ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል እና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ታመነ ጥር 14 /2017 ዓ/ም የክልሉ ጤና ቢሮ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቴክኒካል ኮሚቴ አዋቅረው ወደ ስራ ሲያስገቡ በአገር ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሰጠውን በመሆኑ በተሳካ ሁኔታ እንዲያስፈጽሙ አደራ ተጥሎባቸዋል ብለዋል።
የተዋቀረው ቴክኒካል ኮሚቴ በጥር 21 ቀን 2017 ለሁለተኛ ጊዜ ባደረገው የአፈጻጸም ግምገማ ለዘመቻው ስኬት በጥሩ ሁኔታ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።
በክልሉ ውስጥ በሚገኙ በአብዛኛው የጤና መዋቅር መሰል ቴክኒካል ኮሚቴ መቋቋሙን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን አሁንም የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ እስከ ቀበሌና ቤተሰብ ድረስ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል በውይይቱ አጽንኦት ተሰጥቷል።
የፖሊዮ ዘመቻ በአገር አቀፍ ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ ሁሉም ዞን፣ወረዳ እና ቀበሌ የሚገኙ የጤና ተቋማት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ቦጋለ ገልጸዋል።