የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ነፃ የህክምና አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም “በጎነት ለጤንነት” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን ቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ተካሄደ ።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙን የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክተሬት ዳይረክቴር ዶክቴር እንዳሌ ሣህሌ እና የቴፒ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኝ ገቦ በጋራ በመሆን በይፋ አስጀምረዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር ዶክቴር እንዳለ ሳህሌ ያደጉ ሀገራት መሠረት ያደረጉት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ መሆኑን ጠቁመው ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሀገር ግንባታና ብልፅግና የሚያመጣዉ ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።
በዞኑ በሚገኙ የጤና ተቋማትና በለሎች የነፃ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዉ በተለያዩ ምክንያቶች በጤና ተቋማት መጥተዉ አገልግሎት ያላገኙ ሰዎች አገልግሎቱን እንድያገኙ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ አክለዉ ገልፀዋል።
የሚሰጡ ነፃ የህክምና አገልግሎቶች የስኳር በሽታ ምርመራና ሊየታ የደም ግፍት ምርመራ የማህፀን በር (ጫፍ) ካንሰር ምርመራ የኤች.አይ.ቪ ምርመራና የምክር አገልግሎቶች እና ለሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ዙሪያ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ይሰጣል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣዉ የማህፀን በር ( ጫፍ) ካንሰር በሽታ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመዉ ሴቶች መጥተዉ እንዲመረመሩና ሊየታ እንድያደርጉ ዶክቴር እንዳሌ ሣህሌ ጥር ያቀረቡ ሲሆን ህክምናዉን በወቅቱ መዉሰድ ካልተቻለ ለሞት የሚዳርግ በሽታ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
አክለዉም የቲቪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዉ ሁለት ሳምንት እና ከዛ በላይ ያላቸዉ ሰዎች አክታ በመስጠት በነፃ ምርመራ ማድረግ ይችላሉ ብለዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር የደም ሊገሳ እና ለሎች ተግባራት በስፋት ይከናወናሉ ብለዋል።
ደም መለገስ ህይወት መስጠት በመሆኑ ደም በመለገስ በደም እጥረት የሚሞቱ ሰዎችን ህይወት መታደግ መቻል አለብን ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክተሬት ዳይረክቴር ዶክቴር እንዳሌ ሣህሌ በተለያዩ ምክንያቶች ህክምና ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች መጥተዉ በነፃ ምርመራና ህክምና ማግኘት እንደምቻል ተናግረዋል።
ዘገባው የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።