በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ44 ቀናት ውስጥ የተሰራ የወባ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ዘመቻ ሥራዎች አፈፃፀም ገመገመ።

እንደ ወረዳችን እየተስተዋለ ያለውን ከፍተኛ የወባ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ በመከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ባቡሎ ተናግሯል።
የወባ በሽታው የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የተደረጉ ርብርብ እና የተቀናጀ የዘመቻ ሥራ አበረታች ቢሆንም ማኅበረሰቡን በተደራጀ ሁኔታ በማሳተፍ ባለቤትነትን በመፍጠር የወባ አስተላላፊ ትንኝ ቁጥጥር ሥራ መሰራት እንዳለበትም ተገምግሟል።
በ44 ቀናት በተደረገው ዘመቻ በ4ቱ የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ምሶሶዎች ማለትም :-የትንኝ ቁጥጥር፣ የወባ በሽታ ቅኝት፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ማሳደግ እና የወባ በሽታ ምርመራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደተመራ አቶ በረከት በአንክሮ ገልጸዋል ።
የወባ ዘመቻ ስራን በተገቢው መንገድ ማከናወን፣ ቋሚና ግዜያዊ የወባ መራቢያ ቦታዎችን መለየት ማፍሰስና ማዳፈን ፣ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም መቆጣጠር ሥራዎች በዋናነት እንደተሰራም ተነስቷል ።
ማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የወባ አስከፊነቱን በውል በመረዳትና መከላከል ላይ ትኩረት በመስጠት አልጋ አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም ከበሽታ ተጠቂነት ራሱን ማዳን መቻል እንዳለበት ተብራርተዋል ።
አፈጻጸም ግምገማው የተለያዩ በስምሪት መስኮች ላይ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ስሆን በጥንካሬ የተሰሩ ሥራዎችን ለማበረታታት እና ያልተዳሰሱ ቀሪ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ለመምራት እንደሚያግዝም ተነግሯል።
በስተመጨረሻም በጉዳዩ ዙሪያ የጠለቀ ውይይት ተደርጎ አንኳር ጥያቄና አስተያየት ተነስቶ ለተነሳው ጥያቄ ከመድረክ በቂ ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶት የጋራ አቋም በመያዝ ጥሩ መግባባት ተፈጥሮ መድረኩ በስኬት ተቋጭቷል።
ዘገባው:-የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው !!!