ጤናማና በአዕምሮ የበለጸገ ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት ጤና ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተገለጸ።
የደቡብ ምዕራብ ህ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ለህጻናት የሚሰጡ መድሀኒቶች እና ምግብ ላይ ለቁጥጥር በተዘጋጀው መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በታርጫ ከተማ ተካህዷል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ጤና እና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ የክልሉ ጤና ቢሮ የህጻናቶች እና ህጻናትን ጤንነት ትን ለማስጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ሰጥተው በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የህጻናት ምግብና መድሀኒት አቅርቦትን አስተማማኝ ለማድረግ ቁጥጥር ለማድረግ ግልጽ የሆነ መመርያ መውጣቱ ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ ሁሉም ሰልጣኞች መመሪያውን ወደ ታች አውርደው ልተግብሩት ይገባል ብለዋል።
አገር ተረካቢ ጤናማና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ ለመፍጠር ህብረተሰቡ ለህጻናት በሚሰጡ ምግቦችና መዲሀኒቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም ገልጸዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶችና ህደጻናት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ወ/ሮ ሰውነት እንየው የመመሪያውን ጽንሰ ሀሳብ ለሰልጣኞች በሰፊው አብራርተው ለተፈጻሚነት ሁሉም ሰልጣኝ የበኩሉን ሚና መወጣት አለበት ብለዋል።
ለውይይት በቀረበው መመሪያ ላይ እንደተገለጸው ማንኛውም በእናቶች እና ህጻናት አገልግሎት መስጫ ውስጥ የተሰማራ የጤና ባቸሙያ ለህጻናት የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን መጠበቅ እንዳቸበት ተጠቅሷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ከተሳተሳተፉት አንዳንዶች እንደገለጹት መመሪያው የህጻናትን ምግብና መድሀኒት ቁጥጥርና ክትትል ለማድረግ ግልጽ የሚያደርግ በመሆኑ ወስደን በስራ ላይ እናውላለን ብለዋል።