ተከታታይነት ያለው የጽዳት ዘመቻ በማድረግ የወባ በሽታን መከላከልና ጽዱ ሚዛን አማን ከተማ ለመፍጠር የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ተባለ።
ተከታታይነት ያለው የጽዳት ዘመቻ በማድረግ የወባ በሽታን መከላከልና ጽዱ ሚዛን አማን ከተማ ለመፍጠር የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ተባለ።
በየሳምንቱ ረቡዕ በዘመቻ በማጽዳት የወባ በሽታን መከላከልና ጽዱ ሚዛን አማንን መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሞገስ ሻምበል ገልጸዋል።
በኩታ ገጠም በአንድ የሚኖሩ ነዋሪዎች በጋራ በማጽዳትና ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን በጋራ በማፋሰስ የወባ ወረርሽኝን በጋራ ልንከላከል ይገባልም ብለዋል አቶ ሞገስ።
በየሳምንቱ ቅዳሜ የነበረው የጽዳት ዘመቻ በስራ ምክንያት በርካታ የህብረተሰብ ክፍል እያሳተፈ ባለመሆኑ በየሳምንቱ ረቡእ እንዲሆን በተወሰነው መሰረት በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ በህብረት ቀበሌ ዘመቻው የተጀመረ ሲሆን በሌሎችም ቀበሌዎችና ቀጠናዎች ዘመቻው ተጀምሯል ተብሏል።
የጽዳትና የማፋሰስና ማዳፈን ስራዎችን በስፋት ህብረተሰቡን በማሳተፍ መስራት ካልተቻለ የወባ ወረርሽኝን ለመቀነስ አስቸጋሪ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም የከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ አይሳ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘገባው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በተጨማሪም የመረጃ ወቅታዊነት እና ጥራት ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል አፕሊኬሽን (ODK) የአጠቃቀም ማብራሪያ ለተወያዮች የተሰጠ ሲሆን ይህ አኘሊኬሽን በተወሰኑ እና በተመረጡ የጤና ተቋማት ውስጥ መረጃን አሰባስቦ በበይነመረም ለመላላክ እንደሚውል ተገልጿል።
የወረርሽኑን የስርጭት አድማስ የህ/ቡ የጤና ስጋት እስከማይሆን ድረስ ለማድረስ ሁሉም በጋራ መስራት እንደሚጠይቅ ተወያዮች ገልጸዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ውይይቱን ሲያጠቃልሉ መንግስት ወርሽኑን ለመከላከል ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይገኛል ብለዋል።
በመንግስት የሚቀርቡ የወባ በሽታ ማከሚያ መድሃኒቶችና መገልገያ ቁሳቁሶች በተለይ የወባ መድሀኒት ስርቆት ለመቆጣጠር የተሰራው ስራ አበረታች ቢሆንም አሁንም በትኩረት መሰራት እንደሚገባ አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል።
ህ/ሰቡ የመከላከሉ ስራ ላይ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በማጠናከር በቀጣይ ቤት ለቤት ክትትልና ድጋፍን መስጠት እንደሚገባም ገልጸዋል።
መረጃ ጥራት እና ወቅታዊነት ማጠናከር ለተጀመረው የመከላከል ስራ ወሳኝ በመሆኑ የተሰሩ ስራዎች ተዓማኒነት ተረጋግጦ ግብረ- መልስ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
የወባ በሽታ ማከምያ መድሀኒት እና የመገልገያ ቁሳቁስ በጤና ኬላ ደረጃ አቅርቦቱን አጠናክሮ ለመቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ግብዓቶችን እየተሟሉ እንደሆነ አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎን ከማጠናከር አንጻር በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እና የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች በመጠቀም ለወባ ትንኝ መራቢያነት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን የማዳፈንና የማፋሰስ ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማድረግ ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር መሰራት ይገባል ብለዋል።
የወባ ጫና በህብረተሰቡ እያስከተለ ካለው የጤና ችግር በተጨማሪ በኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ በመንግስት የጤና ተቋማት የህክምና ግብዓት ተደራሽ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ካሉ በኋላ በዘመቻው ከፍተኛ ትጋት እያገለገሉ የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና ሌሎች ባለሙያዎችንና ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል አቶ ኢብራሂም
በውይይቱ በሳምንቱ በመከላከል ዘመቻ በተከናወኑ በርካታ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ውይይት በማድረግ በጠንካራ እና መሻሻል በሚገቡ ጉዳዮች ለይ ተወያይተው ግብረ መልስ በመስጠት ተጠናቋል።
