የዚህ ወር “ቆይታ ከእኛ ጋር” እንግዳችን ፕሮግራም

 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በክልሉ ስለተከሰተው የወባ ወረርሽኝ፣ የመከላከልና ምላሽ አሰጣጥ እንዲሁም አሁናዊ የወረርሽኝ ሁኔታን በሚመለከት ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል። ያደረግነው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል!

(/) የቆይታ ለእኛ ጋር ፕሮግራም እንግዳ ለመሆን ፍቃደኛ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

አቶ ኢብራሂም ተማም እናንተም ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ
መንግስት ኮሙኒኬሽን (/) አጠቃላይ በክልሉ ስለተከሰተው የወባ ወረርሽኝ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጡን?

አቶ ኢብራሂም:-የወባ ወረርሽኝ በክልሉ ሁሉም አከባቢ ባልተለመደ መልኩ በስፋት ተከስተዋል። የወረርሽኙ ጫና በክልሉ ብቻም ሳይሆን እንደሀገር በከፍተኛ ሁኔታ
የጨመረ ሲሆን በተላይም በምዕራብ የሀገሪቱ ከፍል፣ ደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች በተጠናቀቀው
2016 በጀት ዓመት የወረርሽኙ ክስተት ከ2015 ተመሳሳይ ወቅት ጋር
ስነጻጸር እጅጉን ጨምሯል። በክልላችን ተጨባጭ ደግሞ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ያሉባቸው በዳውሮ ዞን፦ የዛባ ጋዞ ወረዳ፣ ጌና፣ ታርጫ ከተማና ታርጫ ዙሪያ ወረዳ፤ በካፋ ዞን፦ የጊምቦ ወረዳ እና የቦንጋ ከተማ፤ በቤንች ሸኮ ዞን፣ ሚዛን ከተማ፣ ደቡብ ቤንች፤ በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ እንዲሁም በአርብቶአደር አከባቢዎች የሚታወቅ የወባ ወረርሽኝ ክስተትና ስጋት አለ። ባለፉት
12 ወራት የወባ ምርመራ ካደረጉ 9መቶ 60 ሺህ ገደማ ሰዎች ውስጥ 56 ከመቶ የሚሆኑት በደማቸው የወባ በሽታ የተገኘባቸው ሲሆን በተላይም በዚህ ሁለት ወራት ውስጥ በንቅናቄ ምርመራ ከተደረገላቸው 4መቶ 73ሺህ 640 ሰዎች ውስጥ 3መቶ ሶስት ሺህ 129 ወባ የተገኘባቸው ሲሆን የመገኜት ምጣኔውም 64.9 ከመቶ ነው።

/ኮ፡ በክልሉ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ተግባር ምን ይመስላል?

አቶ ኢብራሂም፡ በክልሉ ለተከሰተው የወባ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የምላሽ ሰጪ ግብረሀይል ጭምር ተቋቁሞ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በክልሉ ሁሉም
መዋቅሮች በጤና ተቋማትና ጤና ኬላዎች የሚሰሩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በጤና ኬላዎች ደረጃ የወባ ምርመራና ህክምና
መስጠት ተችሏል። በምክትል የቢሮው ኃላፊዎችና በዳይሬክተረቶች የሚመራ የባለሙያ ቡድን በየደረጃው ያለውን የጤና መዋቅር አመራርና ባለሙያ በማቀናጀት በሁሉም የክልሉ አከባቢ ስምረት በመውሰድ ቀበሌን መሠረት ያደረገ ችግር ፍቺ ድጋፍ እያከናወነ ይገኛል። የክልሉ መንግሥትና መሪው የብልጽግና ፓርቲ የወረርሽኙ ጫና በህብረተሰባችን ላይ ያሚያደርሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቀነስ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በኮማንድ ፖስት የመረጃ ለውጥጥ በማድረግ የወረርሽኙን ምላሽ አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ ነው። በጤና ተቋማት ዘወትር ከሚሰጠው መደበኛ የጤና ትምህርት በተጨማሪ የወባ መልዕክቶችን ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የክልሉ ቋንቋዎች በተለያዩ የሚዲያ
በባህርይው ሴክተር ዘለል በመሆኑ ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የመከላከልና መቆጣጠር ስራው በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው። በክረምት የበጎ አግልግሎት ማዕቀፍ ውስጥ አንዱ የወባ መከላከል ዘመቻ እንዲሆን በማድረግ በየአካባቢው የሚገኙ ጊዜያዊና ቋም የወባ መራቢያ ቦታዎችን በንቅናቄ የማፋሰስና ማዳፈን ውጤታማ ተግባር ማከናወን ተችሏል።

/: በክልሉ የወባ ወረርሽኝ ምርመራና ህክምና እንዲሁም የወባ የመድኃኒት አቅርቦትና አስተዳደር ምን ይመስላል፤ የአልጋ አጎበር ስርጭትና አጠቃቀምስ ምን ይመስል?


አቶ ኢብራሂም፡ የወባ ምርመራን በሚመለከት ለህብረተሰቡን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በጤና ኬላ ደረጃ ፈጣን የወባ መመርመሪያ ኪት በማቅረብ ምርምር
እየተከናወነ ይገኛል። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ማከም የሚችል የኳርተም የቀረበ ሲሆን በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያ ተኝተው ለሚታከሙ ደግሞ
3ሺህ 750 የወባ
ታማም ማከም የሚችል መድኃኒት
አርቱስነትቀርቧል። የወባ ትንኝ በመቆጣጠር የመራባት መጠኑን በመግታት ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ በዋናነት የአልጋ አጎበር ስርጭት ሲሆን በ2015 /ም በ50 ወረዳዎች ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የአልጋ አጎበር የተሰራጨ ሲሆን አንድ አጎበር ለሁለት ዓመት የሚያገለግል በመሆኑ በ2016 አዲስ ስርጭት አልተከናወነም። ይሁን እንጅ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ድጋፍ ክትትል ስራዎች በዚህ ዓመት በትኩረት ተሰርተዋል። በዚህም ከ5መቶ 97 በላይ ቤቶች ላይ መልከታ የተደረገ ሲሆን 70 ከቶ የሚሆኑ የአልጋ አጎበርን በአግባቡ የሚጠቀሙ ሲሆን የተቀረው 30 ከመቶ ወይም በአሀዝ ከ170ሺህ በላይ አባወራ በተገቢው እየተጠቀመ አለመሆኑን በመለየት በጤና ኤክስቴንሽን እና በጤና ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ተደርጓል። ሌላው የወባ መከላከያ መንገድ የቤት ለቤት የኬሚካል እርጭት ሲሆን ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ ውስን ኬሚካል ያለ ቢሆንም በክልላችን ከፍተኛ የወባ ስጋትና ጫና ባለባቸው 66 ቀበሌዎች ወደ 81ሺህ 370 ቤቶች ላይ እርጭት ተከናውኗል። ከዚህም ጋር አብሮ ቤት ለቤት የሚሰጠው 1.7 ሚሊዮን ሊትር የወባ የትንኝ ዕጭ መግደያ ኬሚካል በተለዩ 54 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ በማድረግ ጥቅም ላይ ውሏል።

/: በክልሉ የወባ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር አስካሁን በተሰራው ስራ ምን ውጤት ተገኝ?

አቶ ኢብራሂም: የክልሉ መንግሥት ለወባ ወረርሽኝ መቆጣጠር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ግብረሀይል አቋቋሞ ወደ ተግባር በመግባቱ በተላይ ዋና የወባ መለታለፊያ
መንገዶች የኾኑ ጊዜያዊና ቋሚ ቦታዎችን በየአካባቢው በዘመቻ የማፋሰስና የማዳፈን የሰራው ስራ ውጤታማ በመሆኑ ባለፉት
2 ወራት የወረርሽኙ ጫና ከነበረበት አሁን ላይ 11 ከመቶ ቀንሷል፣ ባለፉት 34 ሳምንታት ከነበረበት ደግሞ 27 ከመቶ ቀንሷል። በተላይ ምርመራና ህክምና ስራው በጤና ኬላ ደረጃ መጀመሩ እንዲሁም በአከባቢ ቁጥጥር የተሰራው ውጤታማ ስራ ለዚህ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ ነበረው።

/: የህገወጥ መድኃኒት ዝውውር ቁጥጥር ምን ይመስላል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተጠያቂነት አሰራርስ እንዴት ይገለጻል?

አቶ ኢብራሂም:በወባ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ላይ ቸልተኝነት ያሳዩ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ በየደረጃው ባሉ አመራሮችና
ባለሙያዎች አስተዳዳራዊ እርምጃዎች እየተወሰደ የሚገኝ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ በህገወጥ የጤና አግልግሎት እና ኮንትሮባንድ የመድኃኒት ንግድ ላይ በተሰማሩ አካላት ላይ አስተማሪ የህግ እርምጃዎች እየተወሰደ ነው።

/: በህብረተሰቡ ዘንድ አልፎ አልፎ የሚነሳው ‹‹ መድኃኒት የተላመደ ወባ›› ስለሚባለው ነገር ምን ይላሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ ምን ጥንቃቄ ማድረግ
አለበት ይላሉ
?
አቶ ኢብራሂም: ለዚህ መላምት መነሻው የኾነው በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ ኮንትሮባንድ መድኃኒት መጠቀም በመሆኑ
የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ፣ የተጠናከረ የህገወጥ መድኃኒት ቁጥጥር ስረዓት በመዘርጋት እንዲሁም በግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረት በማድረግ በተሰራው ስራ
ይህንን አዝማሚያ መቀልበስ ተችሏል። ህብረተሰቡ የህመም ስሜት ስሰማው በአቅራቢያው በሚገኘው ጤና ተቋም በመመርመር የታዘዘለትን መድኃኒት በአግባቡ

መጠቀም አለበት።

አቶ ኢብራሂም: ምንም እንኳን የወባ ወረርሽኝ ጫና ከነበረበት አሁን መቀነስ እያሳየ ቢሆንም ከክረምት ወራት መውጣት ጋር ተያይዞ ልጨምር ስለሚችል ህብረተሰብ
ሳይዘናጋ በአካባቢ ቁጥጥር እንዲሁም አልጋ አጎበር አጠቃቀም ላይ ትኩረት ማድረግ ይጠበቅበታል። በአንዳንድ የክልሉ መዋቅር የመዘናጋት እንዲሁም የመረጃ ጥራት
ችግር ያለ በመሆኑ ተገቢው ትኩረት መሰጠት አለበት። በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች በመንግሥት የጤና ተቋማት የመድኃኒት አጠቃቀምና አስተዳደር ቁጥር ማድረግ
እንዲሁም በህገወጥ መድኃኒት ቁጥጥር ላይ ትግል ማድረግ ይገባል። ህብረተሰቡ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የሚተላለፉ ወቅታዊ የወባ መልዕክቶች በአግባቡ
በመከተል እራሱንና ቤተሰቡን ከወባ ወረርሽኝ መከላከል ይኖርበታል።

በዕድገቱ በዛብህ

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *