|

እየተስፋፋ የመጣውን የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አይካፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እያካሄደ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለፁት በክልሉ የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት እየተስፋፋ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የምርመራና ህክምና ስራዎችን የክልሉ ጤና ቢሮ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ተነግሯል ።
ለኤችአይቪ ኤድስ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ስለ በሽታው መተላለፊያና የመከላከያ መንገዶች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ገልፀዋል።
የባለድርሻ አካላት ትውልዱን ስለ ኤችአይቪ ኤድስ አስከፊነት፣ ስለ መከላከልና መቆጣጠር መንገዶች በሚገባ ማስተማር እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ ኢብራሂም ተማም ይህ እንዲሳካ አደረጃጀቶችን በማሳተፍ የንቅናቄ ተግባሩ በየደረጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በክልሉ እየተስፋፋ ከመጣው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴና ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ታክለው የበሽታው ሽፋን አሁን ካለበትም ሊያሻቅብ የሚችል በመሆኑ የማህበረሰብ ንቅናቄ በየደረጃው በስፋት መካሄድ እንዳለበትም ነው የገለፁት።
የምርመራና ምክር አግልግሎት ስረዓት በማቀናጀት በደማቸው ቫይረሱ የተገኘባቸውን ወገኖች የፀረ ኤድስ ህክምና ማስጀመርና በዘላቂነት ማቋቋምም እንደሚጠበቅ ነው የገለጹት።
በጤና ተቋማት በቀበሌ ደረጃ ጨምሮ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በማሰልጠን የተጠናከረ የምርመራ ስራዎች በቀጣይ የሚጀምሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ በበኩላቸው ከግንዛቤ እጥረት አኳያ እየተስፋፋ የመጣሁን የኤችአይቪ ኤድስ ንቅናቄ በሁሉም መስክ እንደ አዲስ የማነቃነቅ ስራ በመጀመር የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በትጋት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ወጣቱ በኤችአይቪ ኤድስ ላይ ያለውን ግንዛቤ መቀነስ ለበሽታው መስፋፋት መንስኤ እየሆነ መምጣቱን ገልፀው በቀጣይ የተጠናከረ የግንዛቤ ስራ በየማህበራዊ መሠረቱ መስራት የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።
ዶክተር ሳምሶን ተካልኝ የአይካፕ ኢትዮጵያ የክልሉ ዋና ዳይሬክትር በመድረኩ ላይ እንደገለፁት ድርጅቱ የኤች አይቪ ስርጭት እንዳይስፋፋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራ እያከናወነ እንደሚገገኝ ገልጸዋል።
ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ፈጠራ ስራ የሀይማኖት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ መጀመር እንዳለበት አሳስበዋል።
የሁሉም ዞኖች ዋና አፈጉባኤዎችን ጨምሮ የክልል ተቋማትና በደማቸው ቫይረሱ የሚገኝ አካላት በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘገባው የቤንች ሸኮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *